ዮሐንስ 2:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም እንደ አይሁድ ልማድ የሚያነጹባቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአይሁድ የመንጻት ሥርዐት መሠረት፣ ከሰባ ዐምስት እስከ አንድ መቶ ዐሥራ ዐምስት ሊትር የሚይዙ ከድንጋይ የተሠሩ ስድስት ጋኖች በዚያ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አይሁድ የመንጻት ሥርዓት ስለ ነበራቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱ ጋን ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ውሃ ለመያዝ ይችል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። |
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥምቀትም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።
ሙሴ የኦሪትን ትእዛዝ ሁሉ ለመላው ሕዝብ ከነገረ በኋላ፥ የላምና የፍየል ደም ከውኃ ጋር ቀላቅሎ፥ ቀይ የበግ ጠጕርና የስሚዛ ቅጠል ነክሮ መጽሐፈ ኦሪቱንና ሕዝቡን ሁሉ ይረጭ ነበር።