La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 18:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ “አን​ተስ ከእ​ርሱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ካደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ሲሞቅ፣ “አንተ ከርሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፣ “እኔ አይደለሁም” ሲል ካደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። “አንተስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም “አይደለሁም፤” ብሎ ካደ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዚያን ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ ሌሎች ሰዎችም “አንተስ ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም “አይደለሁም” ብሎ ካደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። እንግዲህ፦ “አንተ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፦ “አይደለሁም” ብሎ ካደ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 18:25
13 Referencias Cruzadas  

ሣራም ስለ ፈራች “አል​ሳ​ቅ​ሁም” ብላ ካደች። እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።


ጴጥሮስም ከቤት ውጭ በአጥሩ ግቢ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት ገረድም ወደ እርሱ ቀርባ “አንተ ደግሞ ከገሊላው ከኢየሱስ ጋር ነበርህ፤” አለችው።


ጴጥሮስም በግቢ ውስጥ ወደ ታች ሳለ ከሊቀ ካህናቱ ገረዶች አንዲቱ መጣች፤


በግ​ቢ​ውም ውስጥ እሳት አን​ድ​ደው ተቀ​መጡ፤ ጴጥ​ሮ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጠ።


በእ​ሳ​ቱም ብር​ሃን በኩል ተቀ​ምጦ ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና አየ​ችው፤ እርሱ መሆ​ኑ​ንም ለየ​ች​ውና፥ “ይህም ከእ​ርሱ ጋር ነበር” አለች።


እርሱ ግን፥ “ሴትዮ! የም​ት​ዪ​ውን አላ​ው​ቅም” ብሎ ካደ።