La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም በመጣ ጊዜ ዓለ​ምን ስለ ኀጢ​አ​ትና ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍር​ድም ይዘ​ል​ፈ​ዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሚመጣበትም ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሣል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱ በመጣ ጊዜ ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድም ምክንያት የዓለምን ሰዎች ያጋልጣል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤

Ver Capítulo



ዮሐንስ 16:8
10 Referencias Cruzadas  

ለም​ጹም በቆ​ዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለም​ጹም የታ​መ​መ​ውን ሰው ቆዳ​ውን ሁሉ ከራሱ እስከ እግ​ሮቹ ድረስ እንደ ከደ​ነው ለካ​ህኑ ቢመ​ስ​ለው፤


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


“እኔ በእ​ው​ነት የሚ​ሆ​ነ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ ካል​ሄ​ድሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ ወደ እና​ንተ አይ​መ​ጣ​ምና፤ እኔ ከሄ​ድሁ ግን እር​ሱን እል​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ ኀጢ​ኣት፥ በእኔ አላ​መ​ኑ​ምና ነው፤


ስለ ኀጢ​ኣት ከእ​ና​ንተ የሚ​ወ​ቅ​ሰኝ ማን ነው? እኔ እው​ነት የም​ና​ገር ከሆ​ንሁ ለምን አታ​ም​ኑ​ኝም?


እነ​ርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊ​ና​ቸው ወቅ​ሶ​አ​ቸው ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጀምሮ እስከ ኋለ​ኞቹ ድረስ፥ አን​ዳ​ንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ብቻ​ውን ቀረ፤ ሴት​ዮ​ዪ​ቱም በመ​ካ​ከል ቆማ ነበር።


ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ልባ​ቸው ተከ​ፈተ፤ ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ወን​ድ​ሞቹ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ምን እና​ድ​ርግ?” አሏ​ቸው።


ሁሉም ትን​ቢት ቢና​ገሩ ግን የማ​ያ​ምኑ ወይም አላ​ዋ​ቂ​ዎች ቢመጡ ሁሉ ይከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው የለ​ምን? ሁሉስ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸው የለ​ምን?