የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፤ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱዬም ይፍሰስ፤ ልጅ ወንድሜ ወደ ገነቱ ይውረድ፥ መልካሙንም ፍሬ ይብላ።
ዮሐንስ 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ምሳ አደረጉለት፤ ማርታም ታሳልፍላቸው ነበር፤ አብረውት ምሳ ከበሉትም አንዱ አልዓዛር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ለኢየሱስ ሲባል እራት ተዘጋጀ። ማርታ ስታገለግል፣ አልዓዛር ከርሱ ጋራ በማእድ ከተቀመጡት አንዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም እራት አዘጋጁለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር፤ አልዓዛር ግን ከእርሱ ጋር ከተቀመጡት መካከል አንዱ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ራት አዘጋጁለት፤ ማርታ ታገለግል ነበር፤ አልዓዛርም ከኢየሱስ ጋር በማእድ ቀርበው ከነበሩት አንዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም እራት አደረጉለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር፤ አልዓዛር ግን ከእርሱ ጋር ከተቀመጡት አንዱ ነበረ። |
የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፤ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱዬም ይፍሰስ፤ ልጅ ወንድሜ ወደ ገነቱ ይውረድ፥ መልካሙንም ፍሬ ይብላ።
እርሱም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በነበረ ጊዜ፥ በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡንም ሰብራ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።
ጌታቸው በመጣ ጊዜ እንዲህ ሲያደርጉና ሲተጉ የሚያገኛቸው አገልጋዮች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ወገቡን ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ እየተመላለሰም ያገለግላቸዋል።
የጠራውንም እንዲህ አለው፥ “በበዓል ምሳ ወይም ራት በምታደርግበት ጊዜ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህንና ጎረቤቶችህን፥ ባለጸጎች ባልንጀሮችህንም አትጥራ፤ እነርሱም ይጠሩሃልና፤ ብድርም ይሆንብሃልና።
የሚበልጥ ማንኛው ነው? በማዕድ ላይ የተቀመጠው ነው? ወይስ የሚላላከው? በማዕድ ላይ የተቀመጠው አይደለምን? እነሆ፥ እኔ በመካከላችሁ እንደ አገልጋይ ነኝ።
ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፤ ብዙ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእርሱም ጋር ለምሳ ተቀምጠው የነበሩ ቀራጮችና ኀጢአተኞች፥ ሌሎችም ብዙዎች ነበሩ።
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።