ዮሐንስ 11:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም መካከል ወደ ፈሪሳውያን ሄደው የከሰሱት ነበሩ፤ ጌታችን ኢየሱስ ያደረገውንም ሁሉ ነገሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶቹ ግን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ለፈሪሳውያን ተናገሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሩአቸው። |
ፈሪሳውያንም ሕዝቡ በእርሱ ምክንያት እንደ አጕረመረሙ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ ሎሌዎቻቸውን ላኩ።
ሎሌዎቹም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመለሱ፤ እነርሱም፥ “ያላመጣችሁት ለምንድን ነው?” አሉአቸው።
አንድ ሰውም መጥቶ፥ “ያሰራችኋቸው እነዚያ ሰዎች እነሆ፥ በቤተ መቅደስ ውስጥ ናቸው፤ ቆመውም ሕዝቡን ያስተምራሉ” ብሎ ነገራቸው።