ዮሐንስ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም ሁላችን ከሙላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀበልን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀብለናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ሁላችንም ከሙላቱ ተቀበልን፥ በጸጋ ላይ ጸጋን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ የጸጋ ሙላት እኛ ሁላችን በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀብለናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ |
ታላቅ ተራራ ሆይ፥ አንተ ምንድር ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፣ ሰዎችም፦ ሞገስ፥ ሞገስ ይሁንለት ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል ብሎ ተናገረኝ።
እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
የአንዱ ሰው ኀጢአት ሞትን ካነገሠችው በአንድ ሰው በደልም ሞት ከገዛን፥ የአንዱ ሰው የኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋው ብዛትና የጽድቁ ስጦታ እንዴት እጅግ ያጸድቀን ይሆን? የዘለዓለም ሕይወትንስ እንዴት ያበዛልን ይሆን?
እናንተ ግን ለመንፈሳዊ ሕግ እንጂ ለሥጋችሁ ፈቃድ የምትሠሩ አይደላችሁም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ አድሮ ይኖራልና፤ የክርስቶስ መንፈስ ያላደረበት ግን እርሱ የእርሱ ወገን አይደለም።
በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።