ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ እየያዘ በንጉሡ ዙሪያ ከቤተ መቅደሱ ቀኝ እስከ ቤተ መቅደሱ ግራ ድረስ በመሠዊያውና በመቅደሱ አጠገብ እንዲቆም አደረገ።
ኢዩኤል 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱ ከሌላው ርቆ አይቆምም፤ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ይሮጣሉ፤ በመሣሪያቸው ላይ ይወድቃሉ፤ እነርሱም አይጠፉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸው አይገፋፉም፤ እያንዳንዱ መሥመሩን ጠብቆ ይሄዳል፤ መሥመራቸውን ሳይለቁ፣ መከላከያውን ሰብረው ያልፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በጦር መሣርያ መካከል ያልፋሉ፥ የሚያስቆማቸው ነገር የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ ከሌላው ጋር አይጋፋም፤ እያንዳንዱ መስመሩን አይለቅም፤ የጠላትን መሣሪያ ደምስሰው ያልፋሉ፤ ምንም የሚያግዳቸው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፋም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፥ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም። |
ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ የጦር መሣሪያውን በእጁ እየያዘ በንጉሡ ዙሪያ ከቤተ መቅደሱ ቀኝ እስከ ቤተ መቅደሱ ግራ ድረስ በመሠዊያውና በመቅደሱ አጠገብ እንዲቆም አደረገ።
ሕዝቅያስም ሰውነቱን አጽናና፤ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላዩም ግንብ ሠራበት፤ ከእርሱም በስተውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊትም ከተማ የሚያወጣውን በር አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ አዘጋጀ።
ቅጥሩንም የሚሠሩትና ሸክም ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፤ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር።
እኔና ወንድሞችም፥ ብላቴኖችም በኋላዬም የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ መሣሪያችንን እንደታጠቅን እንሄድ ነበር።
አይራቡም፤ አይጠሙምም፤ አይደክሙም፤ አይተኙም፤ የወገባቸውን መታጠቂያ አይፈቱም፤ የጫማቸውም ማዘቢያ አይበጠስም።
እንደ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፤ እንደ ጦረኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፤ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።