ሳኦልና ዮናታን የተወደዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፤ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፤ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
ኢዩኤል 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፤ እንደ ጦረኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፤ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ተዋጊዎች ድንገት አደጋ ይጥላሉ፤ እንደ ወታደሮችም ቅጥርን ይዘልላሉ፤ ከመንገዳቸውም ሳይወጡ፣ አቅጣጫ ይዘው ይጓዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ጦር ሰዎችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፥ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ጦረኞች ይጋፈጣሉ፤ እንደ ተዋጊዎችም ቅጽርን ይዘላሉ፤ ሁሉም ቀጥ ብለው ወደ ፊት ይጓዛሉ፤ በማመንታት አቅጣጫቸውን አይለውጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ሰልፈኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፥ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም። |
ሳኦልና ዮናታን የተወደዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፤ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፤ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
በዚያም ቀን ዳዊት፥ “ኢያቡሴዎናውያንን የሚመታ ሁሉ፥ ዕውሮችንና አንካሶችን፥ የዳዊትንም ነፍስ የሚጠሉትን ሁሉ በሳንጃ ይውጋቸው” አለ። ስለዚህም፥ “ዕውርና አንካሳ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይግቡ” ተባለ።
በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በእግዚአብሔር በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።
“ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፤ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የእግዚአብሔር ናቸውና መጠጊያዎችዋን አትርፉ።
አንዱ ከሌላው ርቆ አይቆምም፤ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ይሮጣሉ፤ በመሣሪያቸው ላይ ይወድቃሉ፤ እነርሱም አይጠፉም።