ኢዩኤል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ! የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኀይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬአቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም የምድር እንስሶች አትፍሩ፤ የምትሰማሩባቸው መስኮች ለምልመዋል፤ ዛፎችም አፍርተዋል፤ የበለሱና የወይኑ ፍሬ እጅግ የበዛ ሆኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ። |
እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤቱ ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኀይሉ ያወጣቸዋል፤ በመቃብር የሚኖሩ ኀዘንተኞችንም እንዲሁ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
ሰዎችም ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፤ የፈረሱት፥ ባድማ የሆኑት፥ የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል፤ ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ።
እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን?” አለው።
በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።
ነገር ግን ሰላምን እዘራለሁ፣ ወይኑ ፍሬውን ይሰጣል፥ ምድርም አዝመራዋን ታወጣለች፥ ሰማያትም ጠላቸውን ይሰጣሉ፣ ለዚህም ሕዝብ ቅሬታ ይህን ነገር ሁሉ አወርሳለሁ።