እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ቀንን እንዲመግብ፥ ትንሹ ብርሃንም ከከዋክብት ጋር ሌሊትን እንዲመግብ አደረገ።
ኢዮብ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ የአጥቢያ ከዋክብትንም፥ በአዜብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ፈጥሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የድብና የኦሪዮን፣ የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድብ የሚባለውን እና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ሠርቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድብ፥ ኦሪዮንና፥ ፕልያዲስ የተባሉትን ከዋክብት፥ እንዲሁም በደቡብ በኩል ያሉትን የከዋክብት ክምችቶች በሰማይ ላይ ያኖራቸው እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኵል ያሉትን የከዋክብት ማደሪያዎች ሠርቶአል። |
እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ቀንን እንዲመግብ፥ ትንሹ ብርሃንም ከከዋክብት ጋር ሌሊትን እንዲመግብ አደረገ።
ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ከዚያም ሄደን ሬቅዩን ወደምትባል ሀገር ደረስን፤ በማግሥቱም ወጣን፤ ከአንድ ቀንም በኋላ ከጐንዋ ነፋስ በነፈሰ ጊዜ በሁለተኛው ቀን ወደ ፑቲዮሉስ ደረስን።