በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፤ ልብሴም ይጸየፈኛል።
ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣ በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።
በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፥ ልብሴም ይጸየፈኛል።
ይህም ሁሉ ሆኖ አንተ ወደ አዘቅት ትጥለኛለህ፤ የገዛ ልብሴ እንኳ ይጸየፈኛል።
መተላለፌን በከረጢት ውስጥ አትመሃል፥ ኀጢአቴንም ለብጠህባታል።
የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፤ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል።
ኀጢአት ብሠራስ ምን አደርጋለሁ? ትላለህ።
ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፤ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።
ብታጠብ፥ እንደ በረዶም ብነጻ፥ እጆቼንም እጅግ ባነጻ፥
የሚከራከረኝ ሰው ቢሆን ኖሮ፥ ወደ አደባባይ በአንድነት በሄድን ነበር!
የሸረሪቶች ድር ልብስ አይሆንም፤ በሥራቸውም ራሳቸውን አያለብሱም፤ ሥራቸው የግፍ ሥራ ነውና።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙና ብታበዢ፥ በእኔ ፊት በኀጢአትሽ ረክሰሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ርኵሰትንም በላይሽ እጥላለሁ፥ እንቅሽማለሁ፥ ማላገጫም አደርግሻለሁ።