ሰነፎችን ሥር ሰድደው አየኋቸው፥ በድንገትም መኖሪያቸው ጠፋች።
ቂል ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፤ ግን ድንገት ቤቱ ተረገመ።
አላዋቂውን ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥ ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ።
ሞኝ ደርጅቶ ሲኖር አየሁ፤ በእግዚአብሔር ቊጣ በድንገት መኖሪያው ፈራረሰ።
ሰነፍ ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥ ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ።
እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያልፋል፤ እድል ፋንታውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፤
“ኀጢአተኛ ድኅነትን ተስፋ ያደርግ ዘንድ ለምን ደጅ ይጠናል? በእግዚአብሔርስ የማያምን ይድናልን? እንጃ!
ጆሮዬ መርገሜን ትስማ፤ በወገኔም መካከል ክፉ ስም ይውጣልኝ።
አቤቱ፥ የመድኀኒቴ አምላክ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
በመዝሙር መጽሐፍ ‘መኖሪያዉ ምድረ በዳ ትሁን፤ በውስጧም የሚኖር አይኑር፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ’ ተብሎ ተጽፎአልና።