ኢዮብ 41:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ እርሱ ዝም አልልም፥ የኀይል ቃልም እንደ እርሱ ያለውን ይቅር ይለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ እንድትምረው ይለማመጥሃል? በለስላሳ ቃላትስ ይናገርሃል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እመልስለትስ ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማን ነው? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምሕረት እንድታደርግለት ይለምንሃልን? በመልካም አነጋገር ይለምንሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እመልስለትስ ዘንድ መጀመሪያ የሰጠኝ ማን ነው? ከሰማይ ሁሉ በታች ያለው ገንዘቤ ነው። |
አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ፥ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ።