ኢዮብ 40:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ የእግዚአብሔር የፍጥረቱ አውራ ነው። ከተፈጠረም በኋላ መላእክት ሣቁበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤ በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ ከፈጠርኳቸው ፍጥረቶች ሁሉ ኀያል ከእኔ በቀር የሚያሸንፈው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። |
በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።