አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
ኢዮብ 40:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስኪ ልዕልናንና ኀይልን ተላበስ፤ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግርማንና ልዕልናን ተላበስ እንጂ፥ ሞገስንና ክብርን ተጐናጸፍ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ከሆነ ራስህን በግርማ ሞገስ ተቀዳጅ ክብርንና ገናናነትንም ተጐናጸፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅነትና በልዕልና ተላበስ፥ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። |
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከእስራኤል የተረፉትን ያከብርና ከፍ ያደርግ ዘንድ በጌትነቱ ምክር በምድር ላይ ያበራል።
ይህ የሚፈርሰው የማይፈርሰውን በለበሰ ጊዜ፥ የሚሞተውም የማይሞተውን በለበሰ ጊዜ፤ “ሞት በመሸነፍ ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ያንጊዜ ይፈጸማል።