ኢዮብ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቃልህ በሽተኞችን ታስነሣ ነበር፥ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህ የተሰናከሉትን ያነሣ ነበር፤ የሚብረከረከውንም ጕልበት ታጸና ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጉልበት ታጸና ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃሎችህ የሚሰናከሉትን ይደግፉ ነበር፤ የሚብረከረኩትንም ጒልበቶች ታበረታ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር። |
መንገዳቸውን መረመርሁ፤ እንደ አለቃም ሆኜ ተቀመጥሁ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር ኖርሁ፤ በሚያዝኑም ጊዜ በእኔ ይጽናኑ ነበር።
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።