ኢዮብ 39:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራራውን እንደ መሰምሪያው ይመለከተዋል፥ ለምለሙንም ሁሉ ይፈልጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየተራራው ይሰማራል፤ ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራራውን እንደ መሰማርያው ይቃኘዋል፥ ለምለሙንም ሣር በሙሉ ይፈልጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተራሮች ላይ ይሰማራሉ፤ በዚያም ምግብ የሚሆናቸው ለምለም ሣር ይፈልጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተራራውን እንደ መሰምርያው ይመለከተዋል፥ ለምለሙንም ሁሉ ይፈልጋል። |
በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በከንቱ ይጮኻልን? የሚበላውን ፈልጎ አይደለምን? ወይስ በሬ በበረት ውስጥ ገለባ ሳለው ይጮኻልን?
ከእነዚህም በድን የሚወድቅበት ሁሉ ርኩስ ነው፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰባበራል፤ ርኩሳን ናቸውና፤ ለእናንተ ርኩሳን ይሆናሉ።