በሚገናኘው ፍላጻ ላይ ይስቃል። ከሰይፍም ፊት አይመለስም።
ያለ አንዳች ሥጋት፣ በፍርሀት ላይ ይሥቃል፤ ሰይፍ ቢመዘዝበትም ወደ ኋላ አይልም።
በፍርሃት ላይ ይስቃል፥ በጭራሽ አይደነግጥም፥ ሰይፍም አያሸሸውም።
ፍርሀት የሚባል ነገር ከቶ አያውቁም፤ ምንም ነገር አያስደነግጣቸውም፤ ሰይፍ ቢመዘዝባቸው እንኳ ወደ ኋላ አይመለሱም።
በፍርሃት ላይ ይስቃል፥ እርሱም አይደነግጥም፥ ከሰይፍም ፊት አይመለስም።
የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ላይ ትጨክናለች፤ ያለ ፍርሀትም በከንቱ ትሠራለች፤
በዘመንዋ ወደ ላይ ራስዋን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፥ በፈረሱና በፈረሰኛው ትሣለቃለች።
በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል፥ በጕልበቱም ወደ ሜዳ ይወጣል።
ቀስትና ጦር በእርሱ ላይ ይበረታሉ፥
የአለንጋ ድምፅ፥ የመንኰራኵርም ድምፅ፥ የፈረሶችም ኮቴ፥ የፈጣን ሰረገላም ጩኸት ተሰምቶአል፣