በዚያን ጊዜ ተወልደህ ነበርና፥ የዕድሜህም ቍጥር ብዙ ነውና፥ በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም።
ያን ጊዜ ተወልደሃል! ዕድሜህ ትልቅ ነውና፣ አንተስ በርግጥ ሳታውቅ አትቀርም!
በዚያን ጊዜ ተወልደህ ነበርና፥ የዕድሜህም ቍጥር ብዙ ነውና፥ በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም።
ዓለም በተፈጠረ ጊዜ ተወልደህ ስለ ነበረ በእርግጥ ታውቃለህ! ዕድሜህም በጣም የገፋ ነው!
በውኑ ከሰው ቀድመህ የተፈጠርህ ሰው አንተ ነህን? ወይስ ከተራሮች በፊት ተፀነስህን?
“የንጋት ወገግታ በአንተ ተፈጥሮአልን? የአጥቢያ ኮከብስ ትእዛዙን በአንተ ዐውቋልን?
በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን? የበረዶውንስ ቅንጣት ቤተ መዛግብት አይተሃልን?
ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ? ታስተውል እንደ ሆነ ንገረኝ።