ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
ኢዮብ 32:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሊዩስም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ በቍጣው ተቈጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ኤሊሁ እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤሊሁም በነዚህ በሦስቱ ሰዎች አንደበት መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ ቁጣው ነደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስቱ ሰዎች ለኢዮብ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት አለመቻላቸውን በማየቱ እጅግ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤሊሁም በነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ ቍጣው ነደደ። |
ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፥ “እኔ በዕድሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ዕውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።
እንዲህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ ጥጃውንም ዘፈኑንም አየ፤ የሙሴም ቍጣ ተቃጠለ፤ እነዚያንም ሁለቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበራቸው።