እኔ በትዕግሥት ጠበቅሁ እንጂ አልተናገርሁም። እናንተ ዝም ብላችሁ ቆማችሁ፥ አልመለሳችሁምና።”
እንግዲህ እነርሱ መልስ ስላጡ፣ ጸጥ ብለውም ስለ ቆሙ፣ በትዕግሥት ልጠብቅን?
እነርሱ አልተናገሩምና፥ ቆመው ዳግመኛ አልመለሱምና እኔ በትዕግሥት እጠብቃለሁን?
እነሆ! እነርሱ የሚናገሩትን አጥተው ዝም ብለው ቆመዋል፤ ታዲያ፥ እነርሱ ጸጥ ቢሉ፥ እኔም በትዕግሥት መጠባበቅ ይገባኛልን?
ላዳምጣችሁ አይገባኝም፥ ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለችና።
“እናንተ ፈራችሁ፥ ዳግመኛም አልመለሳችሁም፤ ከአፋችሁም ቁም ነገር ጠፋ።
ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፦ “ደግሜ እናገራለሁ።
አላዋቂ ጥበብን ቢጠይቅ ጥበብ ይሆነዋል፤ ዝም የሚል ሰውም ጥበበኛን ይመስላል።
ስለዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ ዝም ይላል።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤