La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 31:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እድል ፋንታ ከላይ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ ርስት ከአ​ር​ያም ምን​ድን ነው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሰው ዕድል ፈንታው፣ ከአርያም ከሁሉን ቻይ አምላክስ ዘንድ ቅርሱ ምንድን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ከላይ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ርስትስ ከአርያም ምንድነው?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ከላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተወሰነው የሰው ዕድል ፈንታ ምንድን ነው? በአርያም ካለው ሁሉን ከሚችል አምላክ፥ የተሰጠው ድርሻስ ምንድን ነው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ከላይ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ርስት ከአርያም ምንድር ነው?

Ver Capítulo



ኢዮብ 31:2
7 Referencias Cruzadas  

መሬት ሥጋ​ዬን ይሸ​ፍ​ነው ይሆን? ደሜስ ይፈ​ስስ ይሆን? የም​ጮ​ህ​በ​ትስ ቦታ አላ​ገኝ ይሆን?


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው እድል ፋን​ታው፥ ከሚ​ያ​የው ከፈ​ጣ​ሪ​ውም የተ​መ​ደበ ርስቱ ይህ ነው።”


የኃ​ጥ​ኣን መብ​ራት ትጠ​ፋ​ለች፤ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ትመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለች። የበ​ቀል ቍጣም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤


“ጥን​ቱን መፈ​ራት በእ​ርሱ ዘንድ ያለ አይ​ደ​ለ​ምን? በከ​ፍ​ታ​ውም ሁሉን ነገር አድ​ራጊ ነው።


ይህች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ እድል ፋንታ ናት፥ ግፈ​ኞ​ችም ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ዘንድ የሚ​ቀ​በ​ሏት ሀብት ናት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን አዲስ ነገር ቢፈ​ጥር፥ ምድ​ርም አፍ​ዋን ከፍታ እነ​ር​ሱን፥ ቤታ​ቸ​ውን፥ ድን​ኳ​ና​ቸ​ውን፥ ለእ​ነ​ር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ብት​ው​ጣ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸ​ውም ወደ ሲኦል ቢወ​ርዱ፥ ያን​ጊዜ እነ​ዚህ ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አስ​ቈጡ ታው​ቃ​ላ​ቸሁ።”


መጋ​ባት በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፥ ለመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ርኵ​ሰት የለ​ውም፤ ሴሰ​ኞ​ች​ንና አመ​ን​ዝ​ሮ​ችን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል።