ኢዮብ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያ ሌሊት ኮከቦች ይጨልሙ፤ ሌሊቱም በጨለማ ይኑር፤ ወደ ብርሃንም አይምጣ፤ የንጋት ኮከብም ሲወጣ አይይ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አጥቢያ ኮከቦቹ ይጨልሙ፤ ብርሃንን እየጠበቀ ይጣ፤ የንጋት ጮራ ሲፈነጥቅ አይይ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጋቱ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚያ ሌሊት አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ የብርሃን ተስፋ አይገኝበት፤ የንጋትም ጮራ አይፈንጥቅበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፥ ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥ የንጋትንም ቅንድብ አይይ፥ |
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።