“የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን?
ኢዮብ 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በእግዚአብሔር እጅ ምን እንዳለ አስተምራችኋለሁ፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውንም አልዋሽም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለ እግዚአብሔር ክንድ አስተምራችኋለሁ፤ የሁሉን ቻዩንም አምላክ ዕቅድ አልሸሽግም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ስለ እግዚአብሔር ሥራዎች አስተምራችኋለሁ፥ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእግዚአብሔር ኀይል ምን ያኽል ታላቅ እንደ ሆነ አስተምራችኋለሁ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ያቀደውንም አልሸሽግባችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፥ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም። |
“የእግዚአብሔርን ፍለጋ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክ ወደ ፈጠረው ፍጥረት ፍጻሜ ትደርሳለህን?
ስሙ ለዘለዓለም ቡሩክ ነው፥ ከፀሓይም አስቀድሞ ስሙ ነበረ፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ ሕዝቡ ሁሉ ያመሰግኑታል።
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።