ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር።
ኢዮብ 26:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሲኦል በረኞች ለእርሱ አደሉ። በትእዛዙም ዐመፀኛውን እባብ ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤ እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም የሚሸሸውን እባብ ወጋች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስትንፋሱ ሰማይን ያጠራል፤ በእጁም ተወርዋሪውን እባብ ይወጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች። |
ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።
ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።