ኢዮብ 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀይሉ ብዛት ቢመጣብኝም እንኳ በቍጣው አያስፈራራኝም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋራ ይሟገት ይሆን? አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታላቅ ኃይሉ ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? ይልቁንም! ማዳመጥ ይበቃው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ይፋረደኝ ይሆን? አይደለም፤ ነገር ግን ነገሬን ያዳምጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኃይሉ ብዛት ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? እንኳን! ያደምጠኝ ነበር። |
ስለ ጠቡ በእሳት አቃጥለው ዘንድ ቀርቃሃና ሣርን ማን በሰጠኝ! አሁንም እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ ዛሬ አደረገ፤ እነርሱ ተቃጥለዋልና።
“እኔ ሕያው ነኝ! በበረታች እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በፈሰሰችም መዓት እነግሥባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።