ኢዮብ 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንድሞችህን መያዣ በከንቱ ወስደሃል፥ የታረዘውንም ልብሱን ገፍፈሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ ሰዎችን ገፍፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሞችህ አላግባብ መያዣ ወስደሃል፥ የታረዙትንም ልብስ ዘርፈሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞችህን ያለ አንዳች ምክንያት በዋስትና አስይዘሃቸዋል፤ ሌሎችንም ልብሳቸውን ገፈህ ራቊታቸውን አስቀርተሃቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድሞችህን መያዣ በከንቱ ወስደሃል፥ የእርዘኞቹንም ልብስ ዘርፈሃል። |
ድሀውንና ችግረኛውን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማም፥ መያዣውንም ባይመልስ፥ ዐይኖቹንም ወደ ጣዖታት ቢያነሣ፥ ርኩስንም ነገር ቢያደርግ፥
ሰውንም ባያስጨንቅ፥ መያዣውንም ባይወስድ፥ ባይቀማም፥ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ፥ ለተራቈተውም ልብስን ቢያለብስ፥
ሰውንም ባያስጨንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያዣውን ቢመልስ፥ ፈጽሞም ባይቀማ፥ ከእንጀራውም ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቈተውንም ከልብሱ ቢያለብስ፤