“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ኢዮብ 22:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሁንም መታገሥ ትችል እንደ ሆነ፥ ፍሬህም ይበጅ እንደ ሆነ እስኪ ጽኑ ሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከርሱም ጋራ ሰላም ይኑርህ፤ በረከትም ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም መልካምን ታገኛለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ ኢዮብ ሆይ፥ ራስህን ለእግዚአብሔር አስገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤ ይህን ብታደርግ መልካም ነገርን ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
አጥንቶች ሁሉ እንዲህ ይሉሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃውን ከሚቀማው እጅ ድሃውንና ችግረኛውንም ከሚነጥቀው እጅ ታድነዋለህ።”
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
በጨለማ ውስጥ “ብርሃን ይብራ” ያለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የክብሩን ዕውቀት ብርሃን በልባችን አብርቶልናልና።
እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን፤ እግዚአብሔርም በእኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል፤ ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
ሁሉ የሚገኝባት፥ ከልቡናና ከአሳብ ሁሉ በላይ የምትሆን የእግዚአብሔር ሰላም በኢየሱስ ክርስቶስ ልባችሁንና አሳባችሁን ታጽናው።