ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።
ኢዮብ 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለም ተስፋ ቈረጡብኝ። ብነሣም በእኔ ላይ ሐሜት ይናገራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ ባዩኝም ቍጥር ያላግጡብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃናት እንኳ አጠቁኝ፥ ብነሣም በእኔ ላይ ይናገራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕፃናት እንኳ ይንቁኛል፤ እኔንም በሚያዩበት ጊዜ ያፌዙብኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃናቶች እንኳ አጠቁኝ፥ ብነሣም በእኔ ላይ ይናገራሉ። |
ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ ለመዘባበት በእኔ ላይ ሳቁ፤ አባቶቻቸውን የናቅሁባቸውና እንደ መንጋዬ ውሾች ያልቈጠርኋቸው ዛሬ ለብቻቸው ይገሥጹኛል።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ ሰው በሰው ላይ፥ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ፥ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይታበያል።