ኢዮብ 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ነገርን እነግራችሁ ነበር፤ ራሴንም በእናንተ ላይ እነቀንቅ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣ የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር፥ የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በአንደበቴ ባበረታታኋችሁና እናንተንም ለማጽናናት ብዙ መናገር በቻልኩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር፥ የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር። |
መንገዳቸውን መረመርሁ፤ እንደ አለቃም ሆኜ ተቀመጥሁ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር ኖርሁ፤ በሚያዝኑም ጊዜ በእኔ ይጽናኑ ነበር።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ከእናንተ ወገን የተሳሳተ ሰው ቢኖር በመንፈስ ቅዱስ የጸናችሁ እናንት እንዳትሳሳቱ ለራሳችሁ እየተጠበቃችሁ፥ እንደዚህ ያለውን ሰው ቅንነት ባለው ልቡና አጽኑት።