ኢዮብ 16:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመሟገት ምነው በቻለ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከጥቂት ዓመታት በኋላ፣ ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔ ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዕድሜዬ ፍጻሜ እየተቃረበ ነው፤ ወደማልመለስበት መንገድ ለመሄድ ጥቂት ዘመን ብቻ ይቀረኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥቂቶች ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔ ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ። |
ሰው የሕይወቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕይወት የሚኖር ቢሆን ዳግመኛ እስክወለድ ድረስ፥ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
በምድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮቹም በአንተ ዘንድ የተቈጠሩ ናቸው፤ ዘመኑንም ወስነህ ትሰጠዋለህ፤ እርሱም ከዚያ አያልፍም።
ከፍ ያለውን ተመልክተው ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፤ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፍሬም ሳይበተን፤ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤቱ ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፤