ኢዮብ 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ልብህስ ለምን ይደፍራል? ዐይኖችህስ ለምን ይገላምጣሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብህ ለምን ይሸፍታል? ዐይንህንስ ምን ያጕረጠርጠዋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልብህስ ለምን ወደ ሌላ ይወስድሃል? ዐይኖችህስ ለምን ይገላምጣሉ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልብህ ለምን ወደ ሌላ ይወስድሃል? ስለምንስ በቊጣ ዐይኖችህን ታፈጣለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልብህስ ለምን ይወስድሃል? ዓይኖችህስ ለምን ይገለምጣሉ? |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።