ኢዮብ 14:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን ኀጢአቶችን ቈጥረሃል፤ ከበደሌም እንዲቱንስ እንኳ አልረሳህም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ በርግጥ ርምጃዬን ትከታተላለህ፤ ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፥ ይልቁንም ኃጢአቴን ባልተጠባበቅህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ አሁን እርምጃዬን ሁሉ ትከታተላለህ፤ ሆኖም ኃጢአቴን አታስብብኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፥ ኃጢአቴንም ትጠባበቃለህ። |
እግዚአብሔር በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰው ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።