ኢዮብ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነፋስ እንደ ረገፈ ቅጠል ታፍሰኛለህን? ወይስ ነፋስ እንደሚወስደው ዕብቅ ታሳድደኛለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን? የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የረገፈውን ቅጠል ታስደነግጣለህን? ወይስ የደረቀውን ገለባ ታሳድዳለህን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፋስ እንደሚያረግፈው ቅጠልና እንደ ደረቅ ገለባ ለምን በማስፈራራት ታሳድደኛለህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን? ወይስ የደረቀውን ዕብቅ ታሳድዳለህን? |
ብዙዎች አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏፏቴ ውስጥ በኀይል እንደሚወርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮኻሉ፤ ያጠፉታልም፤ እነርሱም ከሩቅ ይወርዳሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፥ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው እንደ መንኰራኵር ትቢያም ይበተናሉ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ፤