ነገሬን ስሙ ስሙ፥ እኔ በጆሮአችሁ እነግራችኋለሁና።
ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤ እኔ የምለውንም ጆሯችሁ በሚገባ ይስማ፤
ነገሬን ተግታችሁ ስሙ፥ ምስክርነቴንም በጆሮአችሁ አድምጡ።
እስቲ የምናገረውን ቃል በጥንቃቄ አድምጡ የማቀርበውንም ማስረጃ ስሙ።
ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኀኒት ይሆንልኛል።
እነሆ፥ ወደ ፍርዴ ቀርቤአለሁ። ጽድቄም እንደምትገለጥ አውቃለሁ።
“አሁን የአፌን ክርክር ስሙ፥ የከንፈሬንም ፍርድ አድምጡ።
“እኛ አጽናናነው እንዳትሉኝ፥ ስሙ፤ ቃሌን ስሙ።
የሚያደምጠኝን ማን በሰጠኝ! የእግዚአብሔርንም እጅ አልፈራሁ እንደ ሆነ፥ የሚያስፈርድብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖረኝ!
“ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፥ ነገሬንም አድምጥ።