ዝም በሉ፤ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፤ ከቍጣዬም ልረፍ።
“ዝም በሉ፤ እኔ ልናገር፤ የመጣው ይምጣብኝ።
“ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥ የፈለገ ነገር ይምጣብኝ።
እስቲ ዝም በሉ እኔም እንድናገር ዕድል ስጡኝ ከዚያ በኋላ የፈለገው ነገር ይሁን።
ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥ የሆነው ነገር ይምጣብኝ።
“ነፍሴ ስለ ተጨነቀች ቃሌን በእንጕርጕሮ አሰማለሁ፤ ነፍሴም እየተጨነቀች በምሬት እናገራለሁ።
ምሳሌያችሁ እንደ አመድ ዐላፊ ነው፤ ሥጋችሁም እንደ ትቢያ ነው።
ላዳምጣችሁ አይገባኝም፥ ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለችና።
እናገር ዘንድ ዝም በሉ፤ ከተናገርሁ በኋላ ትስቁብኛላችሁና፤
ስለዚህም እኔ አፌን አልከለክልም፤ በመንፈሴ ጭንቀትን እናገራለሁ፤ የነፍሴንም ምሬት በኀዘን እገልጣለሁ።