La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 12:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሕ​ያ​ዋን ሁሉ ነፍስ፥ የሰ​ውም ሁሉ መን​ፈስ በእጁ ናትና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የፍጥረት ሁሉ ሕይወት፣ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ ናት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕይወት ያለው ፍጥረት ሁሉና የእያንዳንዱም ሰው ነፍስ በእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት።

Ver Capítulo



ኢዮብ 12:10
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሰውን ከም​ድር አፈር ፈጠ​ረው፤ በፊ​ቱም የሕ​ይ​ወት እስ​ት​ን​ፋ​ስን እፍ አለ​በት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።


እኔም እነሆ፥ ከሰ​ማይ በታች የሕ​ይ​ወት ነፍስ ያለ​ውን ሥጋ ሁሉ ለማ​ጥ​ፋት በም​ድር ላይ የጥ​ፋት ውኃን አመ​ጣ​ለሁ፤ በም​ድር ያለው ሁሉ ይጠ​ፋል።


እስ​ት​ን​ፋሴ በእኔ ውስጥ ገና ሳለች፥ የሚ​ያ​ና​ግ​ረ​ኝም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በአ​ፍ​ን​ጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥


“ኀጢ​አ​ተኛ ድኅ​ነ​ትን ተስፋ ያደ​ርግ ዘንድ ለምን ደጅ ይጠ​ናል? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ የማ​ያ​ምን ይድ​ና​ልን? እንጃ!


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፈጠ​ረኝ፥ ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ እስ​ት​ን​ፋስ ያስ​ተ​ም​ረ​ኛል።


ውኃ​ቸ​ውን ደም አደ​ረገ፥ ዓሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደለ።


ምድ​ራ​ቸው በን​ጉ​ሦ​ቻ​ቸው ቤቶች ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን አወ​ጣች።


ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድ​ቃ​ንና ጠቢ​ባን ሥራ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያ​ው​ቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታ​ቸው ነው።


ሰማ​ይን የፈ​ጠረ፥ የዘ​ረ​ጋ​ውም፥ ምድ​ር​ንና በው​ስ​ጥዋ ያለ​ውን ሁሉ ያጸና፥ በእ​ር​ስዋ ላይ ለሚ​ኖሩ ሕዝብ እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ለሚ​ሄ​ዱ​ባ​ትም መን​ፈ​ስን የሚ​ሰጥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


“መን​ፈስ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ የሁ​ሉ​ንም ነፍስ ፈጥ​ሬ​አ​ለ​ሁና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ቀ​ስ​ፋ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊ​ዜም አል​ቈ​ጣ​ች​ሁም።


እነ​ር​ሱም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው፥ “የነ​ፍ​ስና የሥጋ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢ​አት ቢሠራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በማ​ኅ​በሩ ላይ ይሆ​ና​ልን?” አሉ።


ከሥጋ የተ​ወ​ለደ ሥጋ ነውና፤ ከመ​ን​ፈ​ስም የተ​ወ​ለደ መን​ፈስ ነውና።


እር​ሱም ሕይ​ወ​ት​ንና እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ሌላ​ው​ንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰ​ጣ​ልና እንደ ችግ​ረኛ የሰው እጅ አያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ውም።


እኛ በእ​ርሱ ሕይ​ወ​ትን እና​ገ​ኛ​ለን፤ በእ​ር​ሱም እን​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሳ​ለን፤ በእ​ር​ሱም ጸን​ተን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም፦ ‘እኛ ዘመ​ዶቹ ነን’ የሚሉ ፈላ​ስ​ፎች አሉ።