ኢዮብ 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብዙ እንደምትናገር እንዲሁ መስማት አለብህ። ወይስ በንግግርህ ብዛት ጻድቅ የምትሆን ይመስልሃልን? ከሴቶች የሚወለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በውኑ ነገር ለሚያበዛ መልስ መስጠት አይገባምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ ጻድቅ ይቈጠራልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለዚህ ሁሉ ከንቱ ቃል መልስ የሚሰጥ የለምን? አንድ ሰው ይህን ያኽል በመለፍለፍ ትክክለኛ ሊሆን ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ለቃል ብዛት መልስ መስጠት አይገባምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ ጻድቅ ይቈጠራልን? |
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መሥዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመሥራት ዐዋቂዎች አይደሉምና።
የኤፌቆሮስን ትምህርት ከተማሩ ፈላስፋዎች መካከልና ረዋቅያውያን ከሚባሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላስፎችም የተከራከሩት ነበሩ፤ እኩሌቶችም፥ “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይፈልጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎችም፥ “ስለ ኢየሱስ ከሙታን ስለ መነሣቱም ሰብኮላቸዋልና የአዲስ አምላክ ትምህርትን ያስተምራል” አሉ።