የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ፤
ጥቂት የሆነው ዘመኔ እያለቀ አይደለምን? ከሥቃዬ ፋታ እንዳገኝ ተወት አድርገኝ፤
የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? በዚህች አጭር ዘመን ጥቂት እንድደሰት እባክህ ተወኝ!
የሕይወቴ ዘመን ጥቂት አይደለምን?
እንዳልነበረስ ለምን አልሆንሁም? ከማኅፀንም ወደ መቃብር ለምን አልወረድሁም?
እጅህን ከእኔ አርቅ፤ ግርማህም አታስደንግጠኝ።
“ከሴት የተወለደ ሟች ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ነው፥ የቍጣ መከራንም የተሞላ ነው።
እኛ የትናንት ብቻ ነን ምንም አናውቅም፤ ሕይወታችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና
እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፤ ነገር ግን መራራ ነገርን አጥግቦኛል።
አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት።
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።