ኢዮብ 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይንም ሳያየኝ ለምን አልሞትሁም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ታዲያ ለምን ከማሕፀን አወጣኸኝ? ምነው ዐይን ሳያየኝ በሞትሁ ኖሮ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክ ሆይ! ስለምን እንድወለድ አደረግኸኝ? ማንም ሳያየኝ ብሞት መልካም በሆነ ነበር! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ። |
እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ።
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር፤” አለ።