የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።
ኤርምያስ 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከሩ አልፎአል፤ በጋውም ዐልቋል፤ እኛም አልዳንንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መከሩ አልፎአል፥ በጋው ተፈጽሟል፥ እኛም አልዳንም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም “እነሆ የመከር ወራት አለፈ፤ በጋውም ተፈጸመ፤ እኛ ግን አልዳንም!” በማለት ይጮኻሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም። |
የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። ሰነፍ ልጅ ግን ራሱን ተገዥ ያደርጋል። ብልህ ልጅ ከቃጠሎ ይድናል፤ ኀጢአተኛ ልጅ ግን በአውድማ ነፋስ የሚጨብጥ ይሆናል። ብልህ ልጅ በመከር ጊዜ ይሠራል። ሰነፍ ልጅ ግን በመከር ጊዜ ይተኛል።
እነሆ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተቀረፁ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድን ነው?
በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ወድቄ ተሰብሬአለሁ፤ ጠቍሬማለሁ፤ ራስ ማዞርም ይዞኛል፤ ምጥ እንደያዛትም ሴት በመከራው እጨነቃለሁ።
ባለቤቱ ተነሥቶ ደጁን ይዘጋልና፤ ያንጊዜ ከደጅ ቆመው፦ ‘አቤቱ፥ አቤቱ፥ ክፈትልን’ እያሉ በር ሊመቱ ይጀምራሉ፤ መልሶም፦ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም ይላቸዋል።
አንቺን ይጥሉሻል፤ ልጆችሽንም ከአንቺ ጋር ይጥሉአቸዋል፤ ድንጋይንም በደንጋይ ላይ አይተዉልሽም፤ የይቅርታሽን ዘመን አላወቅሽምና።”