በሁለቱም አዕማድ በነበሩት ጕልላቶች ላይ በመርበቡ ሥራ አጠገብ ሮማኖቹን አደረገ። ሮማኖቹም በአንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁለተኛውም ጕልላት እንዲሁ ነበረ።
ኤርምያስ 52:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስተ ውጭም ዘጠና ስድስት ሮማኖች ነበሩ፤ በመርበቡም ዙሪያ የነበሩ ሮማኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘጠና ስድስቱ ሮማኖች ከጐን በቀላሉ የሚታዩ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ በዙሪያው ካለው ጌጥ በላይ ያለው የሮማኖች ቍጥር አንድ መቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስተ ውጭም በኩል ዘጠና ስድስት ሮማኖች ነበሩ። በመረበቡም ዙሪያ የነበሩ ሮማኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስተውጪ በኩል ዘጠና ስድስት የሮማን ፍሬ ቅርጾች የነበሩ ሲሆን በመረቡ ዙሪያ መቶ የሮማውያን ፍሬ ቅርጾች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስተ ውጭም ዘጠና ስድስት ሮማኖች ነበሩ። በመረበቡም ዙሪያ የነበሩ ሮማኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ። |
በሁለቱም አዕማድ በነበሩት ጕልላቶች ላይ በመርበቡ ሥራ አጠገብ ሮማኖቹን አደረገ። ሮማኖቹም በአንዱ ወገን ሁለት መቶ ነበሩ። የሁለተኛውም ጕልላት እንዲሁ ነበረ።
በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ ሮማኖችን አድርግ፤ በእነዚያም መካከል በዙሪያው በተመሳሳይ ቅርጽ የወርቅ ሮማኖች ሻኵራዎችን አድርግ፤