እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በደሴቶችዋ ይመካሉና ሰይፍ በውኆችዋ ላይ አለ፤ እነርሱም ይደርቃሉ።
ኤርምያስ 51:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ ጣዖቶቿን የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምድሯም ሁሉ፤ ቍስለኞች ያቃስታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምቀጣበት በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጋው የሚያቃስትበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ የተቀረጹትን ምስሎችዋ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጉት ያንቋርራሉ። |
እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናትና፥ እነርሱም በደሴቶችዋ ይመካሉና ሰይፍ በውኆችዋ ላይ አለ፤ እነርሱም ይደርቃሉ።
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎንን ምስሎች የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፤ ምድርዋም ሁሉ ትደርቃለች፤ ተዋግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
ቸነፈርንም በአንቺ ላይ፥ ደምንም በጎዳናሽ ላይ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያሽም በላይሽ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልሽ ይወድቃሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
የባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ፤ ግብፅንም ይወጋበታል፥ ምርኮዋንም ይማርካል፤ ሰለባዋንም ይሰልባል።