ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
ኤርምያስ 51:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሕዝቤ ሆይ! ከመካከልዋ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ ሆይ፤ ከመካከሏ ውጡ! ሕይወታችሁን አትርፉ! ከአስፈሪው የእግዚአብሔር ቍጣ አምልጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤ ሆይ! ከመካከልዋ ውጡ እያንዳንዱም ሰው ከጌታ ጽኑ ቁጣ ነፍሱን ያድን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ሆይ! ከዚያ ሸሽታችሁ ውጡ! ከሚያስፈራውም ቊጣዬ ሕይወታችሁን ለማትረፍ አምልጡ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቤ ሆይ፥ ከመካከልዋ ውጡ እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ። |
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፥ የመቅደሱንም በቀል፥ በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን ሀገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።
“ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ! ሂዱ፤ አትቁሙ፤ በሩቅ ያላችሁም እግዚአብሔርን አስቡ፤ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
ባቢሎንን ፈወስናት፥ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ከዋክብትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንተዋት፤ ሁላችንም ወደ ሀገራችን እንሂድ።
ማኅበሩንም፥ “ከእነዚህ ክፉዎች ሰዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ” ብሎ ተናገራቸው።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።