እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
ኤርምያስ 5:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምትሰቀጥጥና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኗል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሠቃቂና አስደንጋጭ ነገር በምድሪቱ ላይ ሆኖአል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሠቃቂና አስደንጋጭ የሆነ ነገር በዚህች ምድር ላይ ተፈጽሞአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር በምድር ላይ ሆናለች፥ |
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእስራኤል ድንግል ያደረገችውን በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር የሚሰሙት እንዳለ አሕዛብን ጠይቁ።”
በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥን ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ፤ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁሉም እንደ ሰዶም፥ የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።