ስለዚህ ምድር ትውጣቸዋለች፤ በእርስዋ የተቀመጡ በድለዋልና፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ይቸገራሉ፤ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
ኤርምያስ 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እንደዚህ ያለ ቃል ተናግራችኋልና እነሆ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፤ ትበላቸውማለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቡ ይህን ቃል ስለ ተናገረ፣ ቃሌን በአፍህ ውስጥ የሚፋጅ እሳት፣ ይህንም ሕዝብ ማገዶ አደርጋለሁ፤ እሳቱም ይበላቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸዋለችም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ እንዲህ በመናገራቸው፥ ቃሌ በአፍህ እንደ እሳት ይሆናል፤ ሕዝቡም እንደ እንጨት ሆነው እሳቱ ይበላቸዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸውማለች። |
ስለዚህ ምድር ትውጣቸዋለች፤ በእርስዋ የተቀመጡ በድለዋልና፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ይቸገራሉ፤ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።