La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 41:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም የተ​ገኙ ዐሥር ሰዎች ቀር​በው እስ​ማ​ኤ​ልን እን​ዲህ አሉት፥ “በሜ​ዳው ድልብ አለ​ንና፥ ገብ​ስና ስንዴ፥ ዘይ​ትና ማርም አለ​ንና አት​ግ​ደ​ለን፤” እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው መካ​ከል እነ​ር​ሱን መግ​ደል ተወ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተገደሉት ጋራ የነበሩ ዐሥር ሰዎች ግን እስማኤልን፣ “እባክህ አትግደለን! በዕርሻችን ውስጥ የሸሸግነው ስንዴና ገብስ፣ የወይራ ዘይትና ማር ስላለን እባክህን አትግደለን” አሉት። እርሱም ተዋቸው፤ ከሌሎቹም ጋራ አልገደላቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእነዚያ ሰማኒያ ሰዎች መካከል በተለይ ዐሥሩ ሰዎች “እባክህ አትግደለን! እኛ በእርሻ ውስጥ የደበቅነው ብዙ ስንዴ፥ ገብስ፥ የወይራ ዘይትና ማር. አለን” ብለው እስማኤልን ለመኑት። እርሱም ምሕረት አደረገላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመካከላቸውም እስማኤልን፦ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን የሚሉት አሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 41:8
9 Referencias Cruzadas  

ሰይ​ጣ​ንም መልሶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ቍር​በት ስለ ቍር​በት ነው፤ ሰው ያለ​ውን ሁሉ ስለ ሕይ​ወቱ ይሰ​ጣል።


ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።


በስ​ም​ህም የም​ጠ​ራህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨ​ለማ የነ​በ​ሩ​ትን መዛ​ግ​ብት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ የማ​ይ​ታ​የ​ው​ንም የተ​ደ​በ​ቀ​ውን ሀብት እገ​ል​ጥ​ል​ሃ​ለሁ።


እስ​ማ​ኤ​ልም ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣ​ለ​በት ጕድ​ጓድ ንጉሡ አሳ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ባኦ​ስን ስለ ፈራ የሠ​ራው ጕድ​ጓድ ነበረ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን ሞላ​በት።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?