ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፥ “ሂድ፤ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ።
ኤርምያስ 41:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናታንያም ልጅ እስማኤል ከመሴፋ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ፤ በተገናኛቸውም ጊዜ፥ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታንያ ልጅ እስማኤል ሊገናኛቸው እያለቀሰ ከምጽጳ ወጣ፤ ሲያገኛቸውም፣ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ፤ በተገናኛቸውም ጊዜ፦ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እስማኤል ከምጽጳ እያለቀሰ ሊቀበላቸው ወጣ፤ ወደ እነርሱም በቀረበ ጊዜ “የአሒቃም ልጅ ወደ ሆነው ወደ ገዳልያ ኑ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ፥ በተገናኛቸውም ጊዜ፦ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ አላቸው። |
ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፥ “ሂድ፤ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ።
“በዚያም ወራት በዚያም ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው ይመጣሉ፤ እያለቀሱም መንገዳቸውን ይሄዳሉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ።