የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።
ኤርምያስ 41:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራዊቱንም ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገባዖንም ባለው በብዙ ውኃ አጠገብ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሊወጉ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው በታላቁ ኵሬ አጠገብ ደረሱበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቻቸውንም ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ለመዋጋት ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው ታላቅ ኲሬ አጠገብ አገኙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ከሰዎቻቸው ሁሉ ጋር አሳደው ገባዖን ውስጥ ባለው ታላቅ ኲሬ አጠገብ ደረሱበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹን ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ፥ በገባዖንም ባለው በታላቁ ውኃ አጠገብ አገኙት። |
የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።
እንዲህም ሆነ፤ ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ የቃርሔን ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆችን ሁሉ ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው።