ኤርምያስ 36:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈው ቃል ያለበትን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ የጻፈው ቃል ያለበትን ብራና ካቃጠለ በኋላ፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኤርምያስ ለባሮክ እየነገረው የጻፈውን ቃላት የያዘውን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የጌታ ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እየነገርኩት ባሮክ የጻፈውን የብራና ጥቅል ንጉሥ ኢዮአቄም ካቃጠለው በኋላ ሌላ የሚጠቀለል ብራና ወስጄ የቀድሞውን ቃል እንደገና እንድጽፈው እግዚአብሔር አዘዘኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ክርስታሱንና ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈውን ቃል ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
ይሁዳም ሦስትና አራት ዐምድ ያህል በአነበበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብርዕ መቍረጫ ቀደደው፤ ክርታሱንም በምድጃ ውስጥ በአለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።
ኤርምያስም የኔርዩን ልጅ ባሮክን ጠራ፤ ባሮክም እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ።